Selected:

Expedition with Emperor Menelik II

$14.95

Expedition with Emperor Menelik II

ዘመቻ ከንጉሥ ምኒልክ ጋር: ኻያ ወራት በሐበሻ ምድር

ISBN Code : 978-1-59-907101-5
Language : Amharic
Format : Paperback
Publication date : 03/01/2018

$14.95

Description

ዘመቻ ከንጉሥ ምኒልክ ጋር: ኻያ ወራት በሐበሻ ምድር

ድርሰት፡ በጄ. -ጂ. ቫንደርሃይም

ትርጕም፡ በግርማ ይ. ጌታኹን

ጄ. -ጂ ቫንደርሃይም «ዘመቻ ከንጉሥ ምኒልክ ጋር»  በተባለ በዚህ መጽሐፋቸው በ19ኛው ምእት ማለቂያ ዓመታት ላይ በዐፄ ምኒልክ ቤተመንግሥት ይካኼድ የነበረውን የዘወትር ሕይወት የሚያሳይ ትረካ- በአውሮፓዊ ዐይን ምስክር የተዘገበ ትረካ ነው።

ቫንደርሃይም የፎቶግራፍ ጥበብ ባለሙያ በመሆናቸው ከንጉሡ ጋር ዐብረው እንዲዘመቱ ተጋብዙ። ዘመቻው ዘመናዊውን የኢትዮጵያን ግዛት ቅርጽ በማስያዝ ረገድ ከረዱ፣ በደቡብ የሀገሪቱ ዳርቻ ከተደረጉ ትልልቅ ዘመቻዎች አንዱ ነበር።

ቫንደርሃይም በንጉሠ-ነገሥቱ ዙሪያ በየዕለቱ የሚከሰተውን ሕይወት እንደ ሥዕል እና እንደ ፎቶግራፍ በሚታይ ዝርዝር ጽሁፍ ይገልጹልናል።  በመጽሐፉ ውስጥ ገንኖ ለሚቀርበው የእውነታ ስሜት ተጨማሪ ተዋፅኦ የሚያደርጉ ስልሳ-ስምንት አስደማሚ ፎቶግራፎች አቅርበዋል። የደራሲው ገለጻ ጥሬውን የቀረበ፣ ብዙውን ጊዜም ከቅርብ ዕውቂያ የመነጨ ነው። ወዲህም በትኵረት ያዩትን ማናቸውንም ነገር ከሞላ ጐደል የሚያካትት ነው።

«ዘመቻ ከንጉሥ ምኒልክ ጋር» ዛሬም ዋጋ አለው፤ ባህላዊ እና ዐፄያዊውን የታሪክ አጻጻፍ እንደገና ለመገምገም የሚረዱ ታላላቅ ኹነቶችን በመግለጹ ብቻ ሳይኾን፣ ለግዛት ማስፋፋት እና ፖለቲካዊ ቍጥጥር ሲባል የተከፈለውን ዋጋ መረዳት ለሚፈልጉ ኹሉ [አስረጂ ምንጭ ጽሑፍ] በመኾኑም። ኢትዮጵያ ውስጥ ጭካኔ የተሞሉ ጭቆናዎች እና ልቅ የኾኑ ግፈኛነቶች በኹሉም አቅጣጫ የሚስፋፉ እና ባለማቋረጥ የሚቀጥሉ ነበሩ። የመንግሥትም ሥረታ፣ ግንባታ እና ልወጣ ኺደቶች በጦርነት እና በተዛማጅ የጭቆና መልኮች ላይ የቆሙ ነበሩ፤ አኹንም ናቸው። [ጦርነት እና ጭቆና]  ለርኃብ እና በጭካኔ ለሚወሰዱ ርምጃዎች የሚያመቹ ኾነው ሳለ፣ ብዙውን ጊዜ ስለድርቅ የሚሰጡ ማብራሪያዎችን እና በሰብአዊ ርዳታ ላይ የሚደረጉ አትኵሮቶችን እንደጭምብል ለብሰው ይደበቃሉ። የጀግንነት ሥራን አወዳሽ የነበሩ ሐሳቦች፣ ኢትዮጵያም ተላብሳ የኖረችው ሚስጥራዊነት በአኹኑ ጊዜ ድርቅን፣ ዐመፃን እና ፍጹም ድኽነት ከሚያሳዩ ምስሎች በስተጀርባ በማፈግፈግ ላይ ናቸው። በጦርነት አማካይነት የተከሰተው የምድሪቱ፣ የሕዝቧ እና የተፈጥሮ ሀብቷ ጥፋት ረግቶ የኖረውን የብሉይ ኪዳኒቷ ኢትዮጵያ ምሁራዊ ገጸ-ምድር ተክቶታል። በራስ ተመክሮ ላይ የተመረኰዘው የቫንደር ሃይም ትረካ ስለዚህ ጥፋት ከበቂ በላይ ማስረጃዎች ያቀርባል።

መጽሐፉ የጭቆና እና የጭካኔ ድርጊቶችን ታሪክ ይተርካል። የጭቆናው መልኮች እና መፈጸሚያ ዘዴዎች የተለያዩ፣ በኹሉም ቦታ የሚገኙ እና አንዱ ከሌላው ጋር የማይጣጣሙ ነበሩ። በጠመንጃ እና በባዕዳን ኀይሎች ተጽእኖ አድገው ፍጹም አሸናፊዎች ኾነዋል። በዘመናዊት ኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የማይለዋወጥ አንድ መርሕ አለ፤ ሰዎች የደረሰባቸውን ስቃይ ወይም የተሰማቸውን ሥጋት በሌሎች ላይ ለማድረስ ዝንባሌ የሚያሳዩበት መርሕ።

Close Menu
×
×

Cart